Advertisement

Recent Videos

TDA Colourfully  inaugurated Awlaelo Secondary School - Wukro and Hawelti Semaetat E-library

HDVS_CATEGORY: Documentary
Views: 169

Who's Online

We have 54 guests and no members online

“ዋነኛው የድህነት ተራራ የሚያፈርሰ መሳርያ ትምህርት ነው፡፡”

መሰስ ዜናዊ

 

            የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ይህ አባባል ሲጠቀሙ ያለምክንያት አልነበረም፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህ ሲሉ በዓለማችን ያለው ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት በመረዳተና በመገንዘብ ይመስለናል፡፡ አባባሉ በቀላል ምክንያቶች ለማስደገፍ የሁለት አገሮች ተሞክሮና ነባራዊ ሁኔታዎች ማየት እንችላለን፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ በመአድን ኃብትና ባላት የቆዳ ስፋት ከአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑ አገሮች አንዷ መሆንዋ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ሆኖም ግን በሰው ሃይል ልማት ወደ ኃላ ከቀሩ አገሮች አንዷ በመሆንዋ፣ አገሪቱ በድህነት አረንቋ ተዘፍቃና በጦርነት እየታመሰች ትገኛለች፡፡ በሌላ በኩል ጃፓን በተበታተኑ ደሴቶች የተመሰረተች ሀገር ስትሆን፣ እዚህ ግባ የሚባል የተፈጥሮ ሃብት እንደሌላት ይታወቃል፡፡  አንዳንድ ፀኃፊዎች “Japan’s Resource is its Resourcelessness” በማለት ይህን ሃቅ ይገልፁታል፡፡ ሆኖም ጃፓኖች የሰው ኃይላቸው ማልማት እንዳለባቸው በመገንዘብና አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰዳቸው፣ በጥቂት ዓመታት የድህነት ካባ ከላይ ላይዋ አውልቃ፣ አሁን ሁለተኛ የአለማችን ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ለመሆን በቅታ እናገኛታለን፡፡

 እላይ ከተገለፁት ሁለት እውነታዎች ለመረዳት እንደሚቻለው፣ ትምህርት የድህነትን ተራራ የመናድ አቅሙ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ያሉት ሃብቶች ባግባቡ ለመጠቀምና ለማስተዳደር የተማረና የለማ የሰው ኃይል መኖር የግድ ነው፡፡ ለዚህም ነው የኢፌዲሪ መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ያለው፡፡ መንግስት የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ፣ ባለፉት 23 ዓመታት ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል፡፡

       የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም ለትምህርት ዘርፍ የሰጠው ትኩረት እንደዚሁ ከፍተኛ ነው፡፡ በክልሉ የነበሩ በጣት የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች በብዙ እጥፍ እንዲጨምሩና የክልሉ የትምህርት ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ኣድርጓል፡፡ የትግራይ ትምህርት ቢሮ በ2005ዓም ባወጣው መረጃ መሰረት፣ በክልሉ 2018 የአንደኛና 148 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ይጠቁማል፡፡ በነዚህ ትምህርት ቤቶች 1,195,965 ተማሪዎች ትምህርታቸው እየተከታተሉ እንደሚገኙም ጥናቱ ያትታል፡፡ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ያፈሩዋቸውና እያፈሩዋቸው ያሉ ተማሪዎች የአገሪቱ መጪ እድል ብሩህ እንደሚሆን ከሚታዩ የልማት እምርታዎች መገንዘብ እንችላለን፡፡

 

የትግራይ ልማት ማህበር ከ25 ዓመታት በፊት ሲቋቋምም፣ እንደመንግስት ሁሉ፣ ለዚህ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በክልሉ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት በማለም ነበር፡፡ በያዘው ራእይና አላማ መሰረትም ማህበሩ እስካሁን 570 ኣንደኛ ደረጃ፣ 27 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና  አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገንብቶና ኣሰፈላጊ ግብኣቶች አሟልቶ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡ ት.ል.ማ ከዚህ በተጨማሪም የኣስተማሪዎች አቅም ለመገንባት በስፋት የተጋ ሲሆን፣ በ12 ከተሞች የህዝብ ቤተ መፃህፍት አቋቁሞና አደራጅቶ ለመንግስትና አካባቢ ህብረተሰብ አስረክቧል፡፡ ት.ል.ማ በትምህርት ዘርፍ ከላይ የተገለፁት በጥቂቱ የሰራ ሲሆን፣ በሌሎች ዘርፎች ማለትም ጤና፣ ቱሪዝም፣ የሴቶች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ ስራ አጥነት መቀነስ ወዘተ ላይም ከፍተኛ ስራዎች ከውኗዋል፡፡ በነዚህ በጎ ስራዎችም ከሶስት ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተጠቃሚ ለመሆን የቻለ ሲሆን፣ ኣሁንም በነዚህ ዘርፎች ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

የትግራይ ልማት ማህበር ሁሌ እንደመሪ ቃሉ የሚጠቀምበት “የትግራይ ልማት ማህበር ሃብቱ ኣባላቱ!!” የሚል አባባል አለ፡፡ ማህበሩ ይህ ሲል ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ይህ ለማለት የሚደፍረውም አባላት የማህበሩ ዋና ምሰሶ መሆናቸው በግልፅ ስለሚታወቅ ነው፡፡ የት.ል.ማ አባላት ባገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ ሲሆኑ፣ ለማህበሩ ስራ መቃናት ካለቻቸው ገቢ በየወሩና አመቱ እየቀነሱ የልማት ማህበሩ ለማጠናከር ሌት ተቀን እየተጉ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ አባላት የሚያዋጡት የቁስ፣ ገንዘብና ሌሎች መዋጮ በተገቢው መንገድ ስራ ላይ ማዋል የማህበሩ ኃላፊነት ነው፡፡ ይህ ከኣባላት የሚገኝ መዋጮ ተኣማኒነትና ግልፅነት በሰፈነበት አኳኃን ለተፈለገው አላማ ለማዋል ማህበሩ ሁሌ በትጋት ይሰራል፡፡ ለዚህም ነው የትግራይ ልማት ማህበር በኣባላቱና ደጋፊዎቹ ከፍተኛ ተአማኒነት ያለው ተቋም ለመሆን የበቃው፡፡

 

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና የትግራይ ልማት ማህበር ባለፉት 23 ዓመታት ከላይ የተገለፀውን ያክል የትምህርት ተቋማት ቢገነቡም አሁንም፣ በትምህርት ተደራሽነትና ደረጃቸው የጠበቁ የትምህርት ተቋማት ከማስፋፋት አንጻር ብዙ የሚቀሩ ስራዎች ኣሉ፡፡ ኣሁንም ተማሪዎች አመቺ ባልሆኑ መቀመጫዎች ተቀምጠው፤ ለንፋስና ብርድ ተጋልጠው፤ በበራሪና ተሳቢ ነፍሳት እየተነደፉ ትምህርታቸው እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ እላይ ከተገለፁ 2018 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 250 የሚሆኑት የሚያስተምሩት በግዚያዊ መማርያ ክፍሎት (ዳሶች) እንደሆኑ፣ በዘርፉ የተደረጉ የቅርብ ግዜ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

 

ይህን ግምት ውስጥ በማስገባትም የትግራይ ልማት ማህበር በሶስት ዓመት (2005 – 2007ዓም) ስትራተጂክ እቅዱ፣ 100 ዳስ ትምህርት ቤቶች ወደ መደበኛና ደረጃቸው ወደ ጠበቁ ትምህርት ቤቶች ለመለወጥ እንደግብ ይዞ ይገኛል፡፡ ይህ ግብ ለማሳካትም ት.ል.ማ እንደአቅጣጫ እየተከተለ ያለው በአገር ውስጥና ውጭ ያሉ ቅርንጫፎች እያንዳንዳቸው አንድ ፕሮጀክት እንዲይዙ ማድረግ ሲሆን፣ እስካሁን ሰላሳ (30) ቅርንጫፎች ፕሮጀክት ይዘው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

 

የትግራይ ልማት ማህበር በአገር ውስጥና ውጭ ስልሳ (60) የሚደርሱ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ እያንዳንዳቸው አንድ ዳስ ትምህርት ቤት ወደ መደበኛ ትምህርት ቤት መለወጣቸው ይታወቃል፡፡ ከላይ እንደተገለፀው በክልሉ የነበረ መጠነ ሰፊ ችግር ሙሉ ለሙሉ መወገድ ባይችልም፣ በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ተችሎዋል፡፡ አሁንም ቅርጫፎቹ፣ የተቀሩት ዳስ ትምህርት ቤቶች ወደ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ለመለወጥ በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

 የትግራይ ልማት ማህበር አዲስ አበባን እንደአንድ ዞንና በ11 ቅርንጫፎች በማደራጀት፣ በመስተዳድሩ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆችና የማህበሩ ደጋፊዎች፣ የበኩላቸው ይወጡ ዘንድ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ የአዲስ አበባ ቅርንጫፎች ናቸው ታድያ በ14 ሚልዮን ብር 10 ትምህርት ቤቶች ለመገንባት የሚያስችላቸው  የስምምነት ፊርማ ጥቅምት 1/2007ዓም መቐለ በሚገኘው ሂል ቶፕስ ሆቴል፣ ትምህርት ቤቶቹ ከሚገነቡባቸው ወረዳ አስተዳዳሪዎችና የት.ል.ማ ዋና ፅሕፈት ቤት  ጋር የተፈራረሙት፡፡

 በፊርማው ስነ - ስርዓት የተገኙት የት.ል.ማ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ታደለ ሓጎስ እንዳሉትም “የትግራይ ልማት ማህበር ዋና ምሶሶው ኣባሉ ነው፡፡ አባላት ካለቻቸው ገቢ በመቀነስ የትግራይ ልማት ማህበር ለሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች ለመደገፍ ሁሌም ይተጋሉ፡፡ ያዋጡት ብር በአግባቡ ለታለመለት ግብ ይውል ዘንድም፣ ት.ል.ማ ሁሌም ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ ይሰራል፡፡ ይህ መስተጋብር የትግራይ ልማት ማህበር ከተጠነሰሰበት ግዜ ጀምሮ እስካሁን እየቀጠለ ያለ ነው፡፡ ስለሆነም የአዲስ አበባ ቅርንጫፎች ያሰባሰቡት ገንዘብ በተለመደው የተቋማችን አሰራር መሰረት ትምህርት ቤቶቹ ለመገንባትና ቶሎ ወደ ስራ እንዲገቡ ያላሳለሰ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡ ዶ/ር ታደለ አያይዘውም በሁሉም ቦታ ሁኖው፣ የማህበሩን የስራ እንቅስቃሴ በባለቤትነት በመውሰድ ያልተቆጠበ ደጋፋቸው እየለገሱ ላሉ አባላት፣ ደጋፊዎችና የልማት ኣጋሮች ያላቸው ምስጋና ገልፀዋል፡፡

 በአዲስ አበባ መስተዳድር የአቅም ግምባታ ቢሮ ኃላፊና የት.ል.ማ አዲስ አበባ ልዩ ዞን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ይሳቅ ግርማይ በፊርማ ስነ - ስርዓቱ እንዳሉት፣ በየትኛውም አካባቢ የሚገኝ የትግራይ ተወላጅ፣ የትግራይ ልማት ማህበር ስራዎች ሊደግፍ ይገባል ካሉ በኃላ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች ድጋፋቸው ከመቼው ግዜ በላይ አጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ ያላቸው እምነት ገልፀዋል፡፡

 

አዲስ አበባ ት.ል.ማ ቅርንጫፍ፣ የተለያየ የኑሮ ደረጃ ያላቸው በርከት ያሉ አባላት እንዳሉት የጠቆሙ አቶ ይሳቅ፣ ሁሉም አባል ከሱ የሚጠበቀው ወርሃዊና አመታዊ መዋጮ በማበርከት ለዚህ የተቀደሰ አላማ አብቅቶናል ካሉ በኋላ፣ ለሁሉም አባላት ያላቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ አቶ ይሳቅ አያይዘውም፣ የተሰበሰበው ገንዘብ ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡባቸው  ወረዳ አስተዳዳሪዎችና የት.ል.ማ ዋና ፅህፈት ቤት ባግባቡ ስራ ላይ ያውሉት ዘንድ አሳስበዋል፡፡

 አዲስ አበባ ት.ል.ማ ቅርንጫፍ ካሁን በፊት 8 የትምህርት ቤቶች ቤተ መጻህፍትና 5 ትምህርት ቤቶች ገምብቶ ለተጠቃሚ ህብረተሰብና መንግስት ማስረከቡን ያስታወሱት ደግሞ፣ በት.ል.ማ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ የአባላት ንቅናቄ አስተባባሪ አቶ ፀጋይ አብርሃ ናቸው፡፡ የት.ል.ማ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ አባላት የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በትምህርት ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለመደገፍ ሁሌም በመትጋት ላይ እንደሚገኙ አቶ ፀጋይ አክለው ገልፀዋል፡፡

 ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡባቸው ወረዳ ኣስተዳዳሪዎች በመወከል ንግግር ያደረጉት የአፅቢ ወምበርታ ኣስተዳዳሪ አቶ ወልዱ መዝገበ ሲሆኑ፣ የትግራይ ልማት ማህበር አባላቱ፣ ደጋፊዎቹና የልማት አጋሮቹ በማስተባበር በክልላችን የሚታዩ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ያደረገው እንቅስቃሴ ከልብ እናመሰግናለን በማለት ለማህበሩ ያላቸው አድናቆት ገልፀዋል፡፡ በነዚህ ወረዳዎች ያለውን የትምህርት ቤቶች እጥረት ተገንዝባችሁ፤ አባላትና ደጋፊዎች አንቀሳቅሳችሁ፤ ይህን የስምምነት ፊርማ ለመፈረምና የማአዝን ድንጋይ ለማኖር የመጣችሁ የአዲስ አበባ ት.ል.ማ ቅርንጫፍ አመራሮች እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

 ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡባቸው ወረዳዎችና የመአዝን ድንጋይ የተቀመጠበት ቀን ቀጥለው የተዘረዘሩት መሆናቸው ለማወቅ ተችሎዋል፡፡

ተቁ

የትምህርት ቤቱ ስም

የሚሰራበት ቦታ

የተመደበለት በጀት

የመአዝን ድንጋይ የቀመጠበት ቀን

የሚሰራው ቅርንጫፍ

ዞባ

ወረዳ

01

ደርግጭ 1 ደረጃ ት/ቤ

ደቡብ

ራያ ኣላማጣ

1,400,000.00

02/02/2007ዓም

ኣራዳ ክፍለ ከተማ

02

ገዘመ 1 ደረጃ ት/ቤ

ደቡብ

ኣላጀ

1,400,000.00

02/02/2007ዓም

ኣዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ

03

ዘንያ 1 ደረጃ ት/ቤ

ደቡብ

እንዳመኾኒ

1,400,000.00

02/02/2007ዓም

የካ ክፍለ ከተማ

04

ሰላም ሰረት 1 ደረጃ ት/ቤ

ደቡብ ምብራቕ

ደ/ተምቤን

1,400,000.00

02/02/2007ዓም

ንፋስ ስልክ ላፍቶ

05

ኣሰርቲ 1 ደረጃ ት/ቤ

ምብራቕ

ኣ/ወንበርታ

1,400,000.00

02/02/2007ዓም

ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ

06

ዓደርዕሞ 1 ደረጃ ት/ቤ

ምብራቕ

ኣ/ወንበርታ

1,400,000.00

02/02/2007ዓም

ቄርቆስ ክፍለ ከተማ

07

ገርዛ 1 ደረጃ ት/ቤ

ማእኸል

ጣ/ኣበርገለ

1,400,000.00

02/02/2007ዓም

ጉለሌ ክፍለ ከተማ

08

ፍረ ስውኣት 1 ደረጃ ት/ቤ

ማእኸል

ቆ/ተምቤን

1,400,000.00

02/02/2007ዓም

ልደታ ክፍለ ከተማ

09

ዓዲ ሽሓቕ 1 ደረጃ ት/ቤ

ሰሜናዊ ምዕራብ

ኣ/ፅምብላ

1,400,000.00

03/02/2007ዓም

ቦሌ ክፍለ ከተማ

10

ማይ ሪማ 1 ደረጃ ት/ቤ

ሰሜናዊ ምዕራብ

ፀለምቲ

1,400,000.00

03/02/2007ዓም

ኣቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ

  

ልምዓት ዓዲ ብደቂ ዓዲ!! 

Share

Intervention Areas

  • Education
  • Health
  • Unemployment Reduction
  • Women Empowerment
  • Sports
  • Culture and art
  • Promoting Tourism

ካብ ኣባህላታት መለስ

"ከምወትሩ፣ ከምህዝቢ፣ ከምስድራ፣ 

ነቓዕ እንተይገደፍኩም ከምእትዓስሉ 

ጥርጥር የብለይን፡፡"

 

መለስዜናዊ

Auditing System

Three Levels of auditing:

1. Audit Committee of the General Assembly

2. Internal Audit

3. Accredited External Accounting Firms